የታላቁ
ሕዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ በተቀመጠና ግንባታው በተጀመረ በሁለተኛ ዓመቱ በአንድ ወገን ሱዳንና ግብጽ በሌላ
ወገን ኢትዮጵያ የተሰለፉበት የዐባይን ውኃ አቅጣጫ መቀየር ተከትሎ በተለያዩ ዌብሳይቶች እየታገዘ በቅርቡ የተፈጠረው
የሚዲያና የዲፕሎማሲ እሰጥ አገባ የኖረው የዐባይ ፖለቲካ ቀውስ በሌላ ገጽታ ደግም እየተከሰተ ነው ያሰኛል፡፡
ባለፈው ሳምንት ግብጽ ካይሮ ውስጥ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተሰብስበው የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉት ግብጻውያን
የመንግሥታቸውን አቋም የሚያራምዱ ባይሆኑም ጉዳዩ ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲመራ መጠየቃቸው የዐባይ ፖለቲካ
በእርግጥም በአዲስ መልክ ለመከሰቱ ተጨማሪ ማረጋገጫ ይሆናል፡፡
የፖለቲካ ውዝግብ የማያጣው ዐባይ አሁን
ደግሞ ባልታሰበ ጊዜና ሁኔታ አዲስ መልክ ይዞ ብቅ እያለ ነው፡፡ ዋናዎቹ የጉዳዩ ተዋናዮች፣ ማለትም የኢትዮጵያ፣
የሱዳንና የግብጽ መንግሥታት በይፋ መሠረታዊ የአቋም ለውጥ አለማድረጋቸው እየታወቀ ጉዳዩ በቀጥታ የማይመለከታቸው
ወገኖች ጉዳዩን ወደ ፖለቲካ አቅጣጫ በመጠምዘዝ ላይ መሆናቸው እየታየ ነው፡፡ ግብጽና ሱዳን አሁን በላው ደረጃ
በዐባይ ውኃ አቅጣጫ መቀየር ዙሪያ ከማንገራገር ያለፈ አዲስ አቋም ይፋ አላደረጉም፡፡
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ
የኢትዮጵያ እጅግ ግዙፉ ፕሮጀክት መሆኑ ከተነገረበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ያለው ወቅት በኢትዮጵያም ሆነ በግብጽ
ፖለቲካ ውስጥ ወሳኝ ለውጦች ተካሂደዋል፡፡ በግብጽ በኩል የግድቡ ግንባታ ሲጀመር የነበረው የአብዮታዊ ለውጥ
እንቅስቃሴ ለጊዜውም ቢሆን እልባት አግኝቶና ምርጫ ተካሂዶ አዲስ ሕጋዊ መንግሥት ተቋቁሟል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል
ደግሞ የሕዳሴው ግድብ ሐሳብ አመንጪ ናቸው የሚባሉት የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም
በመለየታቸው አዲስ መንግሥት ባይባልም አዲስ አመራር ተተክቷል፡፡
በእነዚህ ለውጦች መካከል ግን የሕዳሴው
ግድብ ግንባታ ያለምንም እንከን እየተካሔደ ነው ሲባል ቆይቶ አሁን በቅርቡ የዐባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀየር
ሥራውን ተከትሎ አንዳንድ የፖለቲካ ማዕበሎች እዚህና እዚያ እየተነሡ ለመሆናቸው ባለፈው ሳምንት በአብዛኛው
በአካባቢው ሚዲያዎች የተራመዱት አስተሳሰቦችን ማየት ይቻላል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ምንም እንኳን ግድቡን በተመለከተ
መሠረታዊ ልዩነቶችን የሚፈጥሩ ባይሆኑም ውዝግብ የማያጣው የዐባይ ፖለቲካ አንጻር ሲታዩ ግን ‘እሳት በሌለበት ጢስ
የለምና' ችላ ሊባሉ አይገባም፡፡
አሁን ለተፈጠረው ሁኔታ የግድቡ አቅጣጫ መቀየር መንስኤ ይሁን እንጂ
በእነዚህ አገሮች መካከል ግድቡን አስመልክቶ ገና ሲጀመር ሙሉ በሙሉ መተማመንና መግባት ተፈጥሯል ማለት አይቻልም፡፡
ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግሥት የግድቡ መገንባት በግብጽና በሱዳን የዐባይ ወንዝን የውኃ ድርሻ በተመለከተ
ምንም ዓይነት መቀነስ ወይም ጉዳት እንደማይደርስ ሁለቱን ወገኖች ለማሳመን ያላሰለሰ የዲፕሎማሲ ጥረት ሲያደርግ
ቢቆይም ግብጽና ሱዳን ግን በዚህ ጉዳይ ላይ በይፋ አቋማቸውን ሳያሳውቁ ቆይተዋል፡፡ ይህም የሆነው አንድም እስከ
ቅርብ ጊዜ ድረስ በግብጽ ቋሚ መንግሥት ባለመመሥረቱ ሲሆን፤ከተመሰረተም በኋላ በውስጥ ጉዳዮች ተጠምዶ በመቆየቱ
ነበር፡፡ በሱዳን በኩል ደግሞ በአካባቢው ጉዳዮች አንጻር መንግሥታቸው የግብጽን አቋም የመከተል አዝማሚያ ስላለው
ሁኔውን በዝምታ ሲከታተሉ ቆይተው ነበር፡፡
ከዚያን በፊት ሲካሔዱ የነበሩት የሁለቱ ወገኖች ዲፕሎማሲያዊ
ግንኙነቶችና የልዑካን ልውውጦች ዲፕሎማሲያዊ ይዘት የነበራቸውና በአስተማማኝ ስምምነቶች የተቋጩ ባለመሆናቸው ከልብ
የመነጩ ይሁኑ ወይም ከአንገት በላይ የተደረጉ የእጅ ለእጅ መጨባበጦችና የኮክቴል ግብዣዎች መሆናቸው ሳይለይ ሁለት
ዓመታት አልፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ሲነጋገር የነበረው ደግሞ ከግብጽ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ስለነበረ
በግብጾች በኩል ይገለጹ የነበሩት የመግባባትና የመልካም ምኞትን ፍላጎት መግለጫዎች ባለሥልጣኖቹ ሲለወጡ አብረው
መለወጣቸው የማይቀር ነበር፡፡ ለዚህም ነበር የሕዳሴው ግድብ ግንባታ በተጀመረ አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው
የነበሩት የግብጽ ልዑካን አባባል ትክክለኛውን የግብጽ አቋም አያንጸባርቅም ሲባል የነበረው፡፡
ይሄ
የግብጾች አለመታመን ወይም አቋም የመቀያየር ባሕሪ ታሪካዊ አመጣጥ ያለውና ሥር የሰደደ ከመሆኑ አንጻር ከአካባቢው
ጂኦፖለቲካ ጋር ያለው መስተጋብርና ውጤት አብሮ መታየት የሚገባው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የግብጽ መንግሥት በኢኮኖሚም
ሆነ በፖለቲካ የተጠናከረችና በአፍሪካ ቀንድ ወሳኝ ሚና የምትጫወት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር እንደማይፈልግ ከረጅም ጊዜ
ጀምሮ ሲባልበት የቆየ ጉዳይ ነው፡፡ የግብጽ ፖለቲካ ቢቀየርም ግብጾች በዐባይ ላይ ያላቸው የቆየ አመለካከት
በቀላሉ የሚቀየር አይመስልም፡፡
በአብዮት የተወገደው የሙባረክ አስተዳደር የሕዝቡን አስተያየት ከውስጥ
ችግሮች ወደ ውጭ ጉዳዮች ትኩረት ለማስቀየር ይሞክር የነበረው ደግሞ በዐባይ ጉዳይ ላይ የግብጽ አቋም አይቀየርም
በማለት የዐባይን ጉዳይ የአገሪቱ ህልውና መሠረት አድርጎ በማቅረብ የእያንዳንዱን ግብጻዊ ስሜት በመኮርኮር እንደ
ነበር ይታወቃል፡፡
አሁን ግብጽ ውስጥ አንጻራዊ መረጋጋት ሲፈጠር ደግሞ የሙባረክን ዘመን አመለካከት
የሚያቀነቅኑ ኃይሎች አንገታቸውን ቀና በማድረግ የመሐመድ ሙርሲ መንግሥትን ደካማነት ለማጋለጥ በሚል የግድቡን
መሠራት ከግብጽ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የሚጋጭ በማስመሰል በዋና ዋናዎቹ ሚዲያዎቻቸውና በድረ ገጾቻቸው እያስተጋቡ
ይገኛሉ፡፡ ነገ ደግሞ የሙርሲ መንግሥት የሕዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ወይም ተቃዋሚዎቹን ለማዳከም ሲል በግድቡ ግንባታ
ላይ ሌላ ሳንካ የሚደቅን አቋም የማይዝበት ምክንያት አይኖርም፡፡ ግብጾችን ያመነና ጉም የዘገነ መሆኑ ነው ነገሩ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የሕዳሴውን ግድብ ግንባታ በተመለከተ ለድርድር የማይቀርብ አቋም
እንዳላቸው እስካሁን አረጋግጠዋል፡፡ ይህ ማለት ግን ወደፊት የሚቀረው ጉዞ ሙሉ ለሙሉ የተሳለጠ ይሆናል ማለት
ላይሆን ይችላል፡፡ የሕዳሴ ግድቡን ግንባታ በተመለከተ በግብጽ የፖለቲካ ተቃዋሚ ኃይሎች ግፊትም ሆነ በራሱ በግብጽ
መንግሥት የአቋም ለውጥ ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህ የአቋም መለዋወጥ የሕዳሴ ግድቡን ሥራ ባያስቆመውም በፖለቲካ ለመጥለፍ
የሚደረግ ሙከራ ሊሆን ይችላል፡፡
ስለሆነም በአንድ በኩል የግድቡን ግንባታ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት
ለመፈጸም የገንዘብ ማሰባሰቡንም ሆነ የመስክ ሥራውን ማፋጠን የግድ ይላል፡፡ አሁን ባለበት ደረጃ ለግድቡ
ከሚስፈልገው 80 ቢሊየን ብር ውስጥ የተሰበሰበው ከ15 እስከ18 ቢሊየን ብር ብቻ መሆኑ እንዲሁም ከቻይና የተገኘው
ድጋፍም ከዚህ የማይልቅ መሆኑ በራሱ ወደፊት ትልቅ የገንዘብ እጦት ችግር እንደሚገጥም አመላካች ሊሆን ይችላል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የግድቡ መሠራት ለሦስቱም አገሮች ጠቃሚ ነው የሚለውን የቴክኒክ ኮሚቴውን ውሳኔ በመንግሥታቱ
አካባቢ ብቻ ሳይሆን በግብጽ ሕዝብም ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ያላሰለሰ የዲፕሎማሲና የሕዝብ ግንኙነት ሥራ
መሠራት ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ሊገጥሙ በሚችሉት መለስተኛ የቴክኒክ ችግሮች ዙሪያ ከግብጽ ባለሥልጣኖች ጋር
ለመነጋገር በሩን ክፍት አድርጎ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ድርድር ለመሳብ የላሰለሰ ጥረት ማድረግ የሕዳሴው ግድብ በፖለቲካ
ተጠልፎ እንዳይሰናከል ለማድረግ አማራጭ አይኖረውም፡፡ የዐባይ ልጅ እንደገና ውኃ ሊጠማው አይገባምና።
ርእሰ አንቀፅ
ግድቡ በፖለቲካ ሤራ እንዳይጠለፍ
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ በተቀመጠና ግንባታው በተጀመረ በሁለተኛ ዓመቱ በአንድ ወገን ሱዳንና ግብጽ
በሌላ ወገን ኢትዮጵያ የተሰለፉበት የዐባይን ውኃ አቅጣጫ መቀየር ተከትሎ በተለያዩ ዌብሳይቶች እየታገዘ በቅርቡ
የተፈጠረው የሚዲያና የዲፕሎማሲ እሰጥ አገባ የኖረው የዐባይ ፖለቲካ ቀውስ በሌላ ገጽታ ደግም እየተከሰተ ነው
ያሰኛል፡፡ ባለፈው ሳምንት ግብጽ ካይሮ ውስጥ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተሰብስበው የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉት
ግብጻውያን የመንግሥታቸውን አቋም የሚያራምዱ ባይሆኑም ጉዳዩ ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲመራ መጠየቃቸው
የዐባይ ፖለቲካ በእርግጥም በአዲስ መልክ ለመከሰቱ ተጨማሪ ማረጋገጫ ይሆናል፡፡
የፖለቲካ ውዝግብ የማያጣው
ዐባይ አሁን ደግሞ ባልታሰበ ጊዜና ሁኔታ አዲስ መልክ ይዞ ብቅ እያለ ነው፡፡ ዋናዎቹ የጉዳዩ ተዋናዮች፣ ማለትም
የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብጽ መንግሥታት በይፋ መሠረታዊ የአቋም ለውጥ አለማድረጋቸው እየታወቀ ጉዳዩ በቀጥታ
የማይመለከታቸው ወገኖች ጉዳዩን ወደ ፖለቲካ አቅጣጫ በመጠምዘዝ ላይ መሆናቸው እየታየ ነው፡፡ ግብጽና ሱዳን አሁን
በላው ደረጃ በዐባይ ውኃ አቅጣጫ መቀየር ዙሪያ ከማንገራገር ያለፈ አዲስ አቋም ይፋ አላደረጉም፡፡
የታላቁ
ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ እጅግ ግዙፉ ፕሮጀክት መሆኑ ከተነገረበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ያለው ወቅት በኢትዮጵያም ሆነ
በግብጽ ፖለቲካ ውስጥ ወሳኝ ለውጦች ተካሂደዋል፡፡ በግብጽ በኩል የግድቡ ግንባታ ሲጀመር የነበረው የአብዮታዊ
ለውጥ እንቅስቃሴ ለጊዜውም ቢሆን እልባት አግኝቶና ምርጫ ተካሂዶ አዲስ ሕጋዊ መንግሥት ተቋቁሟል፡፡ በኢትዮጵያ
በኩል ደግሞ የሕዳሴው ግድብ ሐሳብ አመንጪ ናቸው የሚባሉት የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም
በመለየታቸው አዲስ መንግሥት ባይባልም አዲስ አመራር ተተክቷል፡፡
በእነዚህ ለውጦች መካከል ግን የሕዳሴው
ግድብ ግንባታ ያለምንም እንከን እየተካሔደ ነው ሲባል ቆይቶ አሁን በቅርቡ የዐባይን ወንዝ አቅጣጫ የማስቀየር
ሥራውን ተከትሎ አንዳንድ የፖለቲካ ማዕበሎች እዚህና እዚያ እየተነሡ ለመሆናቸው ባለፈው ሳምንት በአብዛኛው
በአካባቢው ሚዲያዎች የተራመዱት አስተሳሰቦችን ማየት ይቻላል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ምንም እንኳን ግድቡን በተመለከተ
መሠረታዊ ልዩነቶችን የሚፈጥሩ ባይሆኑም ውዝግብ የማያጣው የዐባይ ፖለቲካ አንጻር ሲታዩ ግን ‘እሳት በሌለበት ጢስ
የለምና' ችላ ሊባሉ አይገባም፡፡
አሁን ለተፈጠረው ሁኔታ የግድቡ አቅጣጫ መቀየር መንስኤ ይሁን እንጂ
በእነዚህ አገሮች መካከል ግድቡን አስመልክቶ ገና ሲጀመር ሙሉ በሙሉ መተማመንና መግባት ተፈጥሯል ማለት አይቻልም፡፡
ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግሥት የግድቡ መገንባት በግብጽና በሱዳን የዐባይ ወንዝን የውኃ ድርሻ በተመለከተ
ምንም ዓይነት መቀነስ ወይም ጉዳት እንደማይደርስ ሁለቱን ወገኖች ለማሳመን ያላሰለሰ የዲፕሎማሲ ጥረት ሲያደርግ
ቢቆይም ግብጽና ሱዳን ግን በዚህ ጉዳይ ላይ በይፋ አቋማቸውን ሳያሳውቁ ቆይተዋል፡፡ ይህም የሆነው አንድም እስከ
ቅርብ ጊዜ ድረስ በግብጽ ቋሚ መንግሥት ባለመመሥረቱ ሲሆን፤ከተመሰረተም በኋላ በውስጥ ጉዳዮች ተጠምዶ በመቆየቱ
ነበር፡፡ በሱዳን በኩል ደግሞ በአካባቢው ጉዳዮች አንጻር መንግሥታቸው የግብጽን አቋም የመከተል አዝማሚያ ስላለው
ሁኔውን በዝምታ ሲከታተሉ ቆይተው ነበር፡፡
ከዚያን በፊት ሲካሔዱ የነበሩት የሁለቱ ወገኖች ዲፕሎማሲያዊ
ግንኙነቶችና የልዑካን ልውውጦች ዲፕሎማሲያዊ ይዘት የነበራቸውና በአስተማማኝ ስምምነቶች የተቋጩ ባለመሆናቸው ከልብ
የመነጩ ይሁኑ ወይም ከአንገት በላይ የተደረጉ የእጅ ለእጅ መጨባበጦችና የኮክቴል ግብዣዎች መሆናቸው ሳይለይ ሁለት
ዓመታት አልፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ሲነጋገር የነበረው ደግሞ ከግብጽ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ስለነበረ
በግብጾች በኩል ይገለጹ የነበሩት የመግባባትና የመልካም ምኞትን ፍላጎት መግለጫዎች ባለሥልጣኖቹ ሲለወጡ አብረው
መለወጣቸው የማይቀር ነበር፡፡ ለዚህም ነበር የሕዳሴው ግድብ ግንባታ በተጀመረ አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው
የነበሩት የግብጽ ልዑካን አባባል ትክክለኛውን የግብጽ አቋም አያንጸባርቅም ሲባል የነበረው፡፡
ይሄ
የግብጾች አለመታመን ወይም አቋም የመቀያየር ባሕሪ ታሪካዊ አመጣጥ ያለውና ሥር የሰደደ ከመሆኑ አንጻር ከአካባቢው
ጂኦፖለቲካ ጋር ያለው መስተጋብርና ውጤት አብሮ መታየት የሚገባው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የግብጽ መንግሥት በኢኮኖሚም
ሆነ በፖለቲካ የተጠናከረችና በአፍሪካ ቀንድ ወሳኝ ሚና የምትጫወት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር እንደማይፈልግ ከረጅም ጊዜ
ጀምሮ ሲባልበት የቆየ ጉዳይ ነው፡፡ የግብጽ ፖለቲካ ቢቀየርም ግብጾች በዐባይ ላይ ያላቸው የቆየ አመለካከት
በቀላሉ የሚቀየር አይመስልም፡፡
በአብዮት የተወገደው የሙባረክ አስተዳደር የሕዝቡን አስተያየት ከውስጥ
ችግሮች ወደ ውጭ ጉዳዮች ትኩረት ለማስቀየር ይሞክር የነበረው ደግሞ በዐባይ ጉዳይ ላይ የግብጽ አቋም አይቀየርም
በማለት የዐባይን ጉዳይ የአገሪቱ ህልውና መሠረት አድርጎ በማቅረብ የእያንዳንዱን ግብጻዊ ስሜት በመኮርኮር እንደ
ነበር ይታወቃል፡፡
አሁን ግብጽ ውስጥ አንጻራዊ መረጋጋት ሲፈጠር ደግሞ የሙባረክን ዘመን አመለካከት
የሚያቀነቅኑ ኃይሎች አንገታቸውን ቀና በማድረግ የመሐመድ ሙርሲ መንግሥትን ደካማነት ለማጋለጥ በሚል የግድቡን
መሠራት ከግብጽ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የሚጋጭ በማስመሰል በዋና ዋናዎቹ ሚዲያዎቻቸውና በድረ ገጾቻቸው እያስተጋቡ
ይገኛሉ፡፡ ነገ ደግሞ የሙርሲ መንግሥት የሕዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ወይም ተቃዋሚዎቹን ለማዳከም ሲል በግድቡ ግንባታ
ላይ ሌላ ሳንካ የሚደቅን አቋም የማይዝበት ምክንያት አይኖርም፡፡ ግብጾችን ያመነና ጉም የዘገነ መሆኑ ነው ነገሩ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የሕዳሴውን ግድብ ግንባታ በተመለከተ ለድርድር የማይቀርብ አቋም
እንዳላቸው እስካሁን አረጋግጠዋል፡፡ ይህ ማለት ግን ወደፊት የሚቀረው ጉዞ ሙሉ ለሙሉ የተሳለጠ ይሆናል ማለት
ላይሆን ይችላል፡፡ የሕዳሴ ግድቡን ግንባታ በተመለከተ በግብጽ የፖለቲካ ተቃዋሚ ኃይሎች ግፊትም ሆነ በራሱ በግብጽ
መንግሥት የአቋም ለውጥ ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህ የአቋም መለዋወጥ የሕዳሴ ግድቡን ሥራ ባያስቆመውም በፖለቲካ ለመጥለፍ
የሚደረግ ሙከራ ሊሆን ይችላል፡፡
ስለሆነም በአንድ በኩል የግድቡን ግንባታ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት
ለመፈጸም የገንዘብ ማሰባሰቡንም ሆነ የመስክ ሥራውን ማፋጠን የግድ ይላል፡፡ አሁን ባለበት ደረጃ ለግድቡ
ከሚስፈልገው 80 ቢሊየን ብር ውስጥ የተሰበሰበው ከ15 እስከ18 ቢሊየን ብር ብቻ መሆኑ እንዲሁም ከቻይና የተገኘው
ድጋፍም ከዚህ የማይልቅ መሆኑ በራሱ ወደፊት ትልቅ የገንዘብ እጦት ችግር እንደሚገጥም አመላካች ሊሆን ይችላል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የግድቡ መሠራት ለሦስቱም አገሮች ጠቃሚ ነው የሚለውን የቴክኒክ ኮሚቴውን ውሳኔ በመንግሥታቱ
አካባቢ ብቻ ሳይሆን በግብጽ ሕዝብም ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ያላሰለሰ የዲፕሎማሲና የሕዝብ ግንኙነት ሥራ
መሠራት ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ሊገጥሙ በሚችሉት መለስተኛ የቴክኒክ ችግሮች ዙሪያ ከግብጽ ባለሥልጣኖች ጋር
ለመነጋገር በሩን ክፍት አድርጎ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ድርድር ለመሳብ የላሰለሰ ጥረት ማድረግ የሕዳሴው ግድብ በፖለቲካ
ተጠልፎ እንዳይሰናከል ለማድረግ አማራጭ አይኖረውም፡፡ የዐባይ ልጅ እንደገና ውኃ ሊጠማው አይገባምና።
የአዲስ ጉዳይ ርእሰ አንቀፅ
No comments:
Post a Comment