በካሳሁን መብራቱ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን አቦቴ አካባቢ ተወላጅ የሆነው ግለሰብ ሞቷል ተብሎ ቤተሰቦቹ ሃዘናቸውን ከተወጡ በኋላ ዳግም በህይዎት ተቀላቅሏቸዋል።
በ40ዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል ላይ የሚገኘው ይኼው ግለሰብ ፥ የተሻለ ህይወት ፍለጋ ከዛሬ 10 አመት በፊት ከትውልድ ስፍራው በመነሳት ወደ ሃረር በማቅናት በግብርና ስራ ላይ ተሰማርቶ ይኖር እንደነበር ተናግሯል።
ግለሰቡ በአዲሱ የመኖሪያ ስፍራው ላለፉት 10 አመታት ሲኖር ፥ በአካባቢው የስልክ አቅርቦት ባለመኖሩና የቤተሰቦቹን አድራሻ ባለማወቁ ምክንያት ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ ደውሎም ሆነ ደብዳቤ ጽፎ እንደማያውቅም ነው የሚናገረው።
በአንዱ ቀን ከሃረር አካባቢ በተደወለ ስልክ ወንድሙ መሞቱን የተረዳው ታናሽ ወንድሙ ፥ ወደ ስፍራው በማቅናት በወንድሙ መቃብር በመገኘት አልቅሶ የአበባ ጉንጉን ማስቀመጡን ይናገራል።
ከሃረር እንደተመለሰም ለመላው ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቹ በማርዳት በአካባቢው ልማድ መሰረት እድር ተዋጥቶላቸው ፥ እርማቸውን ማውጣታቸውን ገልጿል።
ይሁን እንጅ ግለሰቡ ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ በአልን ለማክበር ወደ ቤተሰቦቹ ሲመጣ ያገኘውን ወንድሙን አምኖ መቀበል እንደቸገረውም ነው ፥ ከባልደረባችን ካሳሁን መብራቱ ጋር ባደረገው ቆይታ የተናገረው።
የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ግለሰብ በሰጠው አስተያየት ፥ ተፈጠረ የተባለው አስተያየት እንዳስገረመው ገልጾ ፤ ወደ መኖሪያ አካባቢው ሲመለስ የመቃብር ስፍራውን ማየት እንደሚፈልግ ተናግሯል።
ይህ ጉዳይ በስም መመሳሰል ወይም ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑንም ነው የተናገረው።
መርዶውን ለቤተሰቦቹ ደውሎ የነገራቸው ግለሰብ በበኩሉ የግለሰቡ በህይዎት መኖር ተዓምር መሆኑን ገልጾ ፥ መሞቱንና በቀብር ስነ ስርአቱ ላይ መገኘቱንም አስረድቷል።
አስተያየቱን በመቀጠልም “የግለሰቡን በህይዎት መኖር በጭራሽ አልቀበልም” ብሏል።
ሞቷል የተባለው ግለሰብ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ እንድ መንፈስ ተቆጥሮ መነጋገሪያነቱ ቢቀጥልም ፥ ለረጅም ጊዜያት የተለያቸውን ቤተሰቦቹን በበዓሉ ዋዜማ ቅዳሜ ተቀላቅሎ በአሉን በሰላም አሳልፏል።

No comments:
Post a Comment