Thursday, May 16, 2013

አንጋፋዋ ድምጻዊ አበበች ደራራ አረፈች

ለረጂም ዓመታት በራስ ቴአትር በድምጻዊነት ስትሰራና ለአድማጮችዋ ዜማዎችን ስታቀርብ ኖራ በስተመጨረሻው ወደ እስራኤል ሀገር ከትማ ስትኖረ የነበረችው ታዋቂዋ ድምጸ መልካሟ አበበች ደራራ ዛሬ ሜይ 16 ቀን ባደረባት ህመም ሳቢያ ሕይወቷ አልፏል፡፡
 
አበበች ደራራ በሕመም ተይዛ ለበርካታ ወቅት በአልጋ ላይ ከመቆየቷም ባሻገር ጨርሶ ከሰዎች ጋር ግንኙነት አቋርጣ በሽታዋን ለብቻዋ ስታስታምም እንደነበረች በቅርብ የሚያውቋት ይናገራሉ፡፡
 
የአበበች ደራራ አስከሬን በኖረችበት የቴል አቪቭ ከተማ በዛሬው እለት ከቀኑ 3.00PM ላይ ወደ ቀብር በወዳጅ ዘመዶች ታጅቦ በመሄድ ሥርአተ ቀብርዋም ይፈጸማል፡፡

አርቲስት ደበበ እሸቱ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳስቀመጠው። /addis neger/

አርቲስት ደበበ እሸቱ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳስቀመጠው።
 
 
"በሉ እንጂ . . .በሉ እንጂ . . . በሉ እንጂ
ልቤን ይዞት ሄዷል ከደጅ
ፍቅር ሌባ ነው የመውደድ
ልቤን ይዞት ሄዷል ከመንገድ . . . . ."
 

No comments:

Post a Comment