Tuesday, March 19, 2013

ወጣቷ ኢትዮጲያዊ በቺካጎ ተገደለች


የ18 ዓመቷ ወጣት ሙና አሊ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ መገኘቷ ታውቋል። ከወላጆቿ ጋር የምትኖረው ወጣት ሙና በሴን ሃይ ስኩል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በማጠናቀቅ ዘንድሮ <ሔሮልድ ዋሽንግተን > ኰሌጅ የመጀመሪያ አመት ተማሪ እንደነበረች ታውቋል። ማርች 9 ቀን በጓደኞቿ ፓርቲ ላይ ለመገኘት ከምሽቱ 9፡00 ሰዓት ከቤት እንደወጣች ሲታወቅ ..በዛው ምሽት ከመኖሪያ ቤቷ ሁለት ብሎክ አለፍ ብሎ በሚገኝ አፓርትመንት ውስጥ ከሌሊቱ 1፡30 ተገድላ ሬሳዋ መገኘቱ ተጠቁሞዋል። አንዳንድ ወገኖች እንደተናገሩት ወጣቷ ጥርሷ እንደወለቀ፣ ፊቷ እንደተቧጨረና አንግቷ አካባቢ በገመድ የመታነቅ ነገር እንደታየ ገልፀዋል። ወጣት ሙና ተገድላ የተገኘችበት ሕንፃ ውስጥ መጥፎ ባህሪ ያላቸው ሰዎች እንደሚኖሩ ሲጠቆም፤ ፖሊስ ምስጢራዊውን ግድያ በማጣራት ላይ መሆኑን ከመግለፅ ውጭ ምንም ያለው ነገር የለም። የሟች ወላጅ አባት አቶ አብዱልሰላም አሊ ፥ « ከባድና አስቸጋሪ ነው» ሲሉ በሃዘን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ከሁለት ወር በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ የ19 ዓመት ወጣት ኢትዮጲያዊ መገደሉና አሁንም ይህ ሁኔታ መደገሙ አነጋጋሪና አስደንጋጭ ሆኗል። ለሙና ቤተሰቦችና ወዳጆች ፈጣሪ መፅናናትን ይስጣቸው! Araya Tesfamariam

No comments:

Post a Comment