Wednesday, March 6, 2013

የ ታላቁ ጸሐፌ ተውኔት እና ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን መፅሀፍ ተመረቀ

ታላቁን ጸሐፌ ተውኔት እና ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን ካጣናቸው ድፍን ሰባት ዓመታት እንደቀልድ ነጎዱ፡፡ የጸጋዬ ሴት ልጆች የአባታቸውን ሰባተኛ ሙት ለማሰብ ከሁለት ሳምንት በፊት አዲስ አበባ ነበሩ፡፡ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ደግሞ ከሀገረ አሜሪካ ጸጋዬን የሚመለከት መልካም ዜና ተበስሯል፡፡

የዜናው ምንጭ ላለፉት 15 ዓመታት ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸውን እና ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መጽሐፍትን ሲያሳትም የቆየው “ጸሐይ ፐብሊሸርስ” ነው፡፡ ይኸው አሳታሚ ድርጅት የሎሬት ጸጋዬን የግል ማስታወሻ (Memoir) በሳምንቱ መጀመሪያ ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ሎይላ ሜሪማውንት ዩኒቨርስቲ በይፋ አስመርቋል፡፡ በገጣሚ፣ ደራሲ እና ተርጓሚ ፋሲል ይትባረክ የተዘጋጀው የግል ማስታወሻ “በባለክንፍ ስንኞች ማረግ” (Soaring on Winged Verse) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ነው፡፡

መጽሐፉ ሎሬት ጸጋዬ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ የተጀመረ ሲሆን ከእርሳቸው ጋር በተደረጉ ጥልቅ እና ተከታታይ ቃለ ምልልሶች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ደራሲው ፋሲል ከባለቅኔው ህልፈት በኋላ በአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ያደረጋቸው ቀጣይ ጥናቶችም የመጽሐፉ አካል ናቸው፡፡ መጽሐፉ ከሎሬት ጸጋዬ የእረኝነት ጊዜ አንስቶ በጥበባዊ ስራዎቻቸው ዓለም አቀፍ እውቅና እስከተጎናጸፉበት ድረስ ያለውን አስገራሚ የሕይወት ጉዟቸውን ያስቃኛል፡፡

በ244 ገጾች የተዘጋጀው መጽሐፍ በ24.95 የአሜሪካን ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ መጽሐፉን በ“ኦንላይን” መግዛት የምትችሉ የአሳታሚ ድርጅቱን ድረ ገጽwww.tsehaipublishers.com ትጎበኙ ዘንድ ይሁን፡፡

ምንጭ፡
Habeshawi Kana
ታላቁን ጸሐፌ ተውኔት እና ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን ካጣናቸው ድፍን ሰባት ዓመታት እንደቀልድ ነጎዱ፡፡ የጸጋዬ ሴት ልጆች የአባታቸውን ሰባተኛ ሙት ለማሰብ ከሁለት ሳምንት በፊት አዲስ አበባ ነበሩ፡፡ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ደግሞ ከሀገረ አሜሪካ ጸጋዬን የሚመለከት መልካም ዜና ተበስሯል፡፡
 
የዜናው ምንጭ ላለፉት 15 ዓመታት ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸውን እና ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መጽሐፍትን ሲያሳትም የቆየው “ጸሐይ ፐብሊሸርስ” ነው፡፡ ይኸው አሳታሚ ድርጅት የሎሬት ጸጋዬን  የግል ማስታወሻ (Memoir) በሳምንቱ መጀመሪያ ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ሎይላ ሜሪማውንት ዩኒቨርስቲ በይፋ አስመርቋል፡፡ በገጣሚ፣ ደራሲ እና ተርጓሚ ፋሲል ይትባረክ የተዘጋጀው የግል ማስታወሻ “በባለክንፍ ስንኞች ማረግ” (Soaring on Winged Verse)  የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ነው፡፡ 
    
መጽሐፉ ሎሬት ጸጋዬ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ የተጀመረ ሲሆን ከእርሳቸው ጋር በተደረጉ ጥልቅ እና ተከታታይ ቃለ ምልልሶች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ደራሲው ፋሲል ከባለቅኔው ህልፈት በኋላ በአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ያደረጋቸው ቀጣይ ጥናቶችም የመጽሐፉ አካል ናቸው፡፡ መጽሐፉ ከሎሬት ጸጋዬ የእረኝነት ጊዜ አንስቶ በጥበባዊ ስራዎቻቸው ዓለም አቀፍ እውቅና እስከተጎናጸፉበት ድረስ ያለውን አስገራሚ የሕይወት ጉዟቸውን ያስቃኛል፡፡ 

በ244 ገጾች የተዘጋጀው መጽሐፍ በ24.95 የአሜሪካን ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ መጽሐፉን በ“ኦንላይን” መግዛት የምትችሉ የአሳታሚ ድርጅቱን ድረ ገጽ www.tsehaipublishers.com ትጎበኙ ዘንድ ይሁን፡፡

1 comment: