ከምርጫ 97 በኋላ በተካሄደው የመጀመሪያው ሊባል በሚችለው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አዛውንቶች፣ ጎልማሶች፣ ወጣቶች፣ ታዳጊዎች ሳይቀር ተሳትፈውበት በሠላም ተገባዷል፡፡ ሰልፈኞቹ ከሠማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት መነሻቸውን በማድረግ በአራት ኪሎ... ወደ ፒያሣ በማቅናት በችርችል ጎዳና አድርገው ወደ ተቃውሞ ሰልፉ ማሳረጊያ ኢትዮ - ኩባ ወዳጅነት መንገድ አቅንተዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 17 ቀን በአፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ህዝባዊ ጥሪ አስተላልፎ ነበር። የተቃውሞ ሰልፉ ለማድረግ የታቀደው የአፍሪካ ህብረት 50ኛ ኣመት በዓሉን በሚያከብርበት ዕለት ነው። ዕለቱን ፓርቲው ለተቃውሞ ሰልፍ የመረጠበትን ምክንያት ስንዲህ ሲል ገልፆ ነበር፡፡ ‹‹የኢትዮጵያን ህዝብ ብሶትና አፈና ለዓለማቀፉ ህብረተሰብ ይበልጥ ግልጽ በማድረግ በኩል አስተዋጽኦ ቀኑ የሚኖረው በመሆኑ ነው፡፡›› ለ 3 ቀናትም ሕዝቡ ጥቁር እንዲለብስ ጥሪ አቅርቦ፣ ሰማያዊ ፓርቲ - ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰቡ ተቋማትና ኢትዮጵያውያን ሁሉ በህጋዊውና ሰላማዊው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቢያቀርብም የተቃውሞ ሰልፉን ማሳወቂያ ደብዳቤውን የሚቀበል ሰው ባለ መገኘቱ እና በኋላም ምክትል ከንቲባው ሰልፉን ከሣምንት በኋላ ማድረግ እንደሚቻላቸው በማሳወቃቸው በዛሬው ዕለቱ የተቃውሞ ሰልፉ ሊከናወን በቅቷል፡፡
በዛሬው ዕለት በተከናወነው የተቃውሞ ሰልፉም፤ የህሊና እስረኞች የሆኑት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ፣ ሰዎችን በዘራቸው እየለዩ ከሚኖሩበት ይዞታቸው ማፈናቀሉ እንዲገታ፣መንግስት በሀይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም እና በሙሰኞች ላይ እርምጃ እንዲወስድና ሌሎችም ጥያቄዎች ቀርበዋል።
በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ሕዝቡ ብሶቱን በስፋት ያሰማ ሲሆኑ በእለቱ ከተንፀባረቁት መፈክሮች መካከል ‹‹የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ባስቸኳይ ይፈቱ!››፣ ‹‹በጥፊ በርግጫ አይገዛም ሐገር››፣ ‹‹መንግስት የለም ወይ››፣ ‹‹ ወኔ የሌለው የሐገር ሸክም ነው፡፡››፣ ‹‹ፍትሕ እያሉ ቃሊቲ ገቡ››፣ ‹‹ውሸት ሰለቸን!››፣ ‹‹የህዝቡን አንድነት እዩ ተመልከቱ››፣ ‹‹ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻን ደም(2) እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም!›› የሚሉ እና ሌሎችም መሰል የሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብትን የሚጠይቁ መፈክሮች ተስተጋብተዋል፡፡
የተቃውሞ ሰልፉ ተሳታፊዎች እጃቸውን በማቆላለፍ ታስረናል ምልክት ያሳዩ ሲሆን ‹‹ሰላማዊ ነን ተቀላቀሉን በማለትም›› ሌሎች ግራ እና ቀኝ ቆመው የነበሩ ሰዎችን ለተቃውሞው ሰልፍ ጋብዘዋል፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የተቃውሞ ሰለፍ በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት አደባባይ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ፣ የህግ ምሁሩና ፓለቲከኛው ዶ/ር ያዕቆብ፣ ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉ ወገኖች ተወካይ እና ሌሎችም ንግግራቸውን በማድረግ ወደ ማገባደጂያው ተቃርቧል፡፡ እስካሁን በደረሰን መረጃ መሰረትም ምንም ዓይነት ሁከት አለመከሰቱን ሪፖርተሮቻችን ከሥፍራው ጠቁመውናል፡፡

No comments:
Post a Comment