አፋኝ ህጎች ይሰረዙ፣ አገራችን አትበታተንም፣ የታሰሩ የህሊናና የፖለቲካ አስረኞች ይፈቱ የሚሉና ሌሎች ተመሳሰይ መፈክሮችን በመያዝ ጎዳና ሞልተው አልፈዋል። ኢትዮጵያ ሃገሬ የሚል ዜማ በማዜምና የመብት ጥያቄዎችን በማስተጋባት የተካሄደ ያለውን ሰለካማዊ ሰልፍ ያዘጋጀው ሰማያዊ ፓርቲ ሲሆን፣ ፓርቲው በእድሜ ከሁሉም ፓርቲዎች ታናሹና በወጣት አመራሮች የሚመራ ነው ። ሰልፉ ከቅንጅት የ1997 ሰልፍ በሁዋላ የተካሄደ ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ የታየበት ነው። ኢህአዴግ ፖርላማውን መሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሬያለሁ በሚልበት ሁኔታ ይህን ያህል ሰፊ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ አዳባባይ መውጣቱ ወደፊት ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ቢዘጋጅ ህዝቡ ጎዳና ሊያጣብብ እንደሚችል የሚያመለካክት ነው።

No comments:
Post a Comment